የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በጉባኤውም የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ተወካዮች፣ የማኀበሩ የሥራ አመራር አባላት፣ የማኀበሩ ባለድርሻ አባላት እና እንግዶች ተገኝተዋል።
የማኀበሩን አባላት ከስድስት መቶ በላይ ያደረሠውና ባለፈው በጀት ዓመት(ጥር 2018)ሥራ የጀመረው ኀብረት ሥራ ማኀበሩ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ብድር መሥጠቱም በጉባኤ ላይ ተገልጿል።
የማኀበሩ ሥራ አመራር ሠብሣቢ ዶክተር እስማኤል ሐሰን ማኀበሩ የአባላትን ጥቅም ለማሥከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ የቁጠባ እና የብድር ተደራሽነት ላይ እየሠራ መሆኑን በመልእክታቸው ገልጸዋል።
በጉባኤውም የማኀበሩ እቅድ እንዲሁም ሪፖርት ቀርቦ ሠፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ባለፉት ወራትም በአባላት ቁጥር መጨመር፣ በቴክኖሎጅ አጠቃቀም፣ በብድር አሠጣጥ እንዲሁም በተቋማዊ ማኔጅመንት፣ ማኀበራዊ ኃላፊነትን በመወጣትና በመሣሠሉት ጉዳዮች ሥኬታማ ሥራዎች መሰራታቸው ተገልጿል።
ኢንፊኒቲ ከአዲስ አበባ ባለፈ በሀገር አቀፍ ደረጃ በክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት የአገልግሎት አድማሱን እያሠፋ ሲሆን የመጀመሪያውን ቅርንጫፉንም በደሴ ከተማ በቅርቡ መክፈቱ ይታወቃል።
ጉባኤውም ያለፈውን በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ተጠናቋል።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።