የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የኅብረት ሥራ የቤተሰብ ቀንን ለመጀመሪያ ጊዜ በደማቅ መርሃግብር አከበረ፡፡

የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የኅብረት ሥራ የቤተሰብ ቀንን ለመጀመሪያ ጊዜ በደማቅ መርሃግብር አከበረ፡፡
የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የኅብረት ሥራ የቤተሰብ ቀንን ለመጀመሪያ ጊዜ በደማቅ መርሃግብር አከበረ፡፡
--------------------------------------------
ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ፣ የኅብረት ሥራ ዘርፍ እንደ ሃገር ትልቅ አጀንዳ አድርጎ በመስራት ትልቅ ስኬት የተገኘበት አመት መሆኑን ተናግረዋል።
የኅብረት ሥራ ማኅበራት ካፒታል ወደ 77.2 ቢሊዮን ብር ማሣደግ መቻሉ እና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቁጠባ ከነበረበት 13.6 ቢሊዮን ወደ 41.4 ማድረስ መቻሉ ይህም ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ተሰራጭቷል ተብሏል፡፡
በኅብረት ሥራ ግብይት ዘርፍም በዓመቱ ከ12 ሺህ በላይ ኅብረት ሥራ ማህበራትን ተሳታፊ በማድረግ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ግብይት ድርሻን በማሳደግ እንዲሁም ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የቀበሌ የኅብረት ሥራ የልማት አመቻች ባለሞያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገልጧል፡፡
የኅብረት ሥራ አዋጅን ማሻሻል፣ የኅብረት ሥራ ስትራተጂ እና ፍኖተ-ካርታ ለህትመት በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱን የስትራተጂክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮሃንስ በቀለ ተናግረዋል።
የ2018 የስኬት ጉዞ በ2019 እንዲቀጥል የተጀመሩትን የሪፎርም ንቅናቄዎች ማጠናከር፣ የአባላትን አመኔታ ማስቀጠልና የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የካፒታል አቅም የበለጠ ማሳደግ የዓመቱ ቁልፍ አቅጣጫዎች ናቸው፡፡
“የ2018 ስኬትን ወደ 2019 የላቀ ውጤት ማሸጋገር” የዕለቱ ዋና መሪ ሀሳብ ነው፡፡ መረጃው የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ነው፡፡
Chat With Us