ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሠረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎችና ወላጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሠረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎችና ወላጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሠረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎችና ወላጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
………………………
የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን በክረምቱ የበጎ ፈቃድ መርሃግብር ኢንፊኒቲን ጨምሮ 10 ከሚሆኑ ኅብረት ሥራ ማህበራት በተገኘ ድጋፍ፣ 80 ለሚሆኑ በኮሚሽኑ ውስጥ እያገለገሉ ላሉ ሰራተኞች ልጆች የትምህርት ቁሳቁሶችን የማከፋፈል እና ማዕድ የማጋራት መርሃግብርም አካሂዷል፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ እንዳሉት ኮሚሽኑ ኅብረት ሥራ ማህበራትን በማስተባበር በርካታ የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ ከ356 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል።
በኮሚሽኑ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሃመልማል ክብሬ በበኩላቸው ማህበራትን በማስተባበር እና ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ በመስራት በተለያዩ ቦታዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን የማከፋፈል እና ማዕድ የማጋራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም በሸገር ሲቲ የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ስራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በኮሚሽኑ ለ200 ተማሪዎች 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ሥለመደረጉ ተገልጿል ::
በሀገራዊ የልማት ሥራዎች ሠፊ ተሣትፎ እያደረገ ያለው ኢንፊኒቲ በሸገር ከተማ በቡራዩ ክ/ከተማና በአማራ ክልል ደሴ ከተማ የችግኝ ተከላ በማድረግ በአረንጓዴ ልማት የላቀ ተሳትፎ አድርጓል፣
ማኀበሩ በደሴ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ ከ25 በላይ ህጻናት የትምህርት ቁሣቁሥ ድጋፍ ማድረጉም ይታወሣል።
ኢንፊኒቲ ከሚሰጠው የፋይናንስ አገልግሎት ባሻገር በሀገራዊ የልማት ሥራዎች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
Chat With Us