የኢንፊኒቲ አመራሮች እና ሠራተኞች የተሣተፉበት የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ያዘጋጀው "ተስፋን እንትከል" የችግኝ ተከላ መርህ ግብር ተካሄደ።

የኢንፊኒቲ አመራሮች እና ሠራተኞች የተሣተፉበት የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ያዘጋጀው "ተስፋን እንትከል" የችግኝ ተከላ መርህ ግብር ተካሄደ።
የኢንፊኒቲ አመራሮች እና ሠራተኞች የተሣተፉበት የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ያዘጋጀው "ተስፋን እንትከል" የችግኝ ተከላ መርህ ግብር ተካሄደ።

ኮሚሽኑ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር በመሆን በሸገር ሲቲ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ነው መርሀ ግብሩን ያካሄደው።

ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰና ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ ኢንፊኒቲን ጨምሮ 20 የቁጠባ እና ብድር እና 15 የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

በፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ ዘንድሮ ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተተከሉ መሆናቸውን ጠቅሰው የአረንጓዴ ልማት ለኅብረት ሥራ ማህበራት ዋነኛ የልማት አጀንዳ እንዲሁም ባህል ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማኀበራዊ ኃላፊነቶቹን እየተወጣ የሚገኘው ኢንፊኒቲ በተናጠልም ሆነ ከሌሎች ተቋማትና አጋሮች ጋር በመሆን በችግኝ ተከላም ሆነ በሌሎች ሀገራዊ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ሁኖ እንደሚሠራ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የማኀበሩ የሥራ አመራርና ማኔጅመንት አባላት አረጋግጠዋል።

የፌደራል ኀብረት ስራ ኮሚሽን በታላላቅ ሀገራዊ የልማት ሥራዎች ኀብረት ሥራ ማኀበራት እንዲሣተፉና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታና የሚደነቅ በመሆኑ በኢንፊኒቲ ስም ምስጋና እናቀርባለን።

ኀብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us