ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ ላይ ተሳተፈ፡፡
-------------------------
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባዘጋጀውና ከሰኔ 12-13/2018 ዓ.ም በሚካሄደው የኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ በርካታ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ከባለድርሻዎቹ አንዱ የሆነውና በፋይናንስ ዘርፉ በአጭር ጊዜ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኘው ኢንፊኒቲ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ እስክንድር መኩሪያ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ምስጋናው አየለ ተሳትፈዋል፡፡
አውደ ርዕዩ "የነቃ ኢንቨስተር= የተጠበቀ ኢንቨስተር" በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄድ ሲሆን በርካታ ምርትና አገልግሎቶችም በኤክስፖው ቀርበው በርካታ ማኅበረሰብም እየጎበኘ ነው፡፡
ዝግጅቱም ጎብኚዎች የካፒታል ገበያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲቃኙ ፣ ስለ ካፒታል ገበያው ግንዛቤ እንዲያገኙ እና በካፒታል ገበያው ካሉ ተዋናዮች ጋር በአካል የሚገናኙበት ዕድል የሚፈጥር ሲሆን እየተካሄደ ያለው በአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ግቢ ነው፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ ማኀበር በኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ ላይ ተሳተፈ፡፡