ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማኀበር በደሴ ከተማ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማኀበር  በደሴ ከተማ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ቁጠባ እና ብድር ኀብረት ስራ ማኀበር በደሴ ከተማ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ኢንፊኒቲ ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በደሴ ከተማ በመክፈት ውጤታማ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

ማኀበሩ ሥምምነቱን የተፈራረመው ከደሴ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማኀበራዊ ጉዳይ መምሪያ፣ ከስራና ክህሎት መምሪያ፣ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ እንዲሁም MBA ከተሠኘ የኤሌክትሪክ ባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪዎች አቅራቢ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ነው።

በስምምነቱም ተቋማቱ የማኀበረሠቡን ችግሮች የሚያቃልሉ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለመሥጠት በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ነው።

የወጣቶችን፣ የሴቶችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊ ችግሮች መፍታት እንዲቻል የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሠሩ የተቋማቱ ተወካዮች በስምምነቱ ወቅት አረጋግጠዋል።

ኢንፊኒቲ "ኀብረት ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ የማህበረሠቡን የቁጠባ እና ብድር ፍላጎት ለማሟላት እየተጋ ያለ እና በአጭር ጊዜ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኝ ሀገራዊ የፋይናንስ ተቋም ነው።
Chat With Us