ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር የመጀመሪያ የክልል ቅርንጫፋን በደሴ ከተማ በይፋ ስራ አስጀመረ፡፡

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር የመጀመሪያ የክልል ቅርንጫፋን በደሴ ከተማ በይፋ ስራ አስጀመረ፡፡
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር የመጀመሪያ የክልል ቅርንጫፋን በደሴ ከተማ በይፋ ስራ አስጀመረ፡፡
በደማቅ ስነ ስርዓት በተካሄደው የስራ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱም የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው፣ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና፣ የማኅበሩ የስራ አመራር አባላት እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ በስራ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንፊኒቲ ቅርንጫፍ መክፈትና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ወደ ውቧ ደሴ ከተማችን መምጣታቸው ለከተማዋ ዕድገት ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
የፋይናንስ ተቋማት መንግስት ለዜጎች የሚፈጥረውን የስራ እድል እና ምቹ ሁኔታ በማገዝ ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፤ በዚህም የፋይናንስ ተቋሙን በማገዝ የከተማ አስተዳደሩ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።
የማህበሩ ስራ አመራር ሰብሳቢ ዶ/ር እስማኢል ሀሰን ከፋና ደሴ ቅርንጫፍ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያ የክልል ቅርንጫፋችንን ደሴ ከተማ ይዘን ስንመጣ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህረሰብ ክፍሎች አማራጭ ብድር በማቅረብ ኢኮኖሚውን መደገፍ ነው። የወለድ አልባው "ኢንፊኒቲ ሂዳያ" አገልግሎታችን ደግሞ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በቅርበት ለመስራትና ኢኮኖሚያዊና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ብለዋል።
የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር መኩሪያ በበኩላቸው ኢንፊኒቲ ኅላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበር በደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ሲከፍት የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በማብዛት ማህበሩ ኀላፊነቱን የበለጠ እንዲወጣ ለማስቻል እንደሆነ አብራርተዋል።
ኢንፊኒቲ መደበኛ ቁጠባ ፣የፈቃድ ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ቁጠባ፣ ወለድ አልባ ቁጠባ፣ ሙዳይ ቀጠባ እና የአደራ ገንዘብ ቁጠባ ወዘተ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ናቸው።
ኢንፊኒቲ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ቅርንጫፍ በመክፈት የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለመስጠት እየተጋ ያለ ሀገራዊ ተቋም ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ክልሎች ቅርንጫፉን እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us