የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሄደ።
ማኀበሩ በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ አይጠየፍ ቀበሌ ሽውሽዋው በተባለ አካባቢ “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ያከናወነው።
ኢንፊኒቲ ኃ/የተወሰነ መ/ ቁጠባና ብድር ህኀብረት ስራ ማህበር የደሴ ቅርንጫፍ ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ባዘጋጁት ፕሮግራም ከ400 በላይ ችግኞች ተተክለዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የኢንፊኒቲ ሥራ አመራር ሰብሳቢ ዶ/ር እስማኤል ሐሰንን ጨምሮ የማኀበሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የደሴ ቅርንጫፍ ሠራተኞችና የማኀበሩ አባላት እንዲሁም የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተሣትፈዋል።
ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከአዲስ አበባ ውጭ በደሴ ከተማ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በይፋ ስራ ማስጀመሩ የሚታወቅ ነው።
ኢንፊኒቲ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ !” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዋነኛ ተዋናይ በመሆን እየሠራ ይገኛል።
ኢንፊኒቲ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከችግኝ ተከላ አረንጓዴ አሻራ ባለፈ ለተቸገሩ ህጻናት የትምህርት ቁሣቁሥ በማበርከት እንዲሁም በደም ልገሣ እና በሌሎችም ማኀበራዊ አገልግሎቶች የበኩሉን እየተወጣ የሚገኝ ሀገራዊ ተቋም ነው።
ኀብረት ለዘላቂ ልማት።
የኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መሰረታዊ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሄደ።