ኢንፊኒቲ ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በደሴ ከተማ ከፍቷል፡፡

ኢንፊኒቲ ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በደሴ ከተማ ከፍቷል፡፡
መልካም ዜና ለደሴ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ
……….
ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር በቅርቡ ተቋቁሞ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኝ ሀገራዊ ተቋም ነው፡፡
ማኅበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ አድማሱን እያሰፋ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በደሴ ከተማ ከፍቷል፡፡
በወሎዋ እምብርት ደሴ ከተማ - ፒያሳ አላሙዲ ህንጻ 3ኛ ፎቅ (ቁጥር-308) ላይ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ማኅበሩ በወለድና ከወለድ ነጻ የመኪና፣ የቤት፣ የቢዝነስ ማስፋፊያ፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የልጆችና ሌሎችንም የቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን እንደሚሰጥም ይፋ አድርጓል፡፡
የደሴ ከተማ ነዋሪዎችም አባል በመሆንና ድርሻ በመግዛት የኅብረት ስራ ማኅበሩ የሚሰጠዉን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ያበስራል፡፡
ኢንፊኒቲ በቅርቡ በማኅበሩ አገልግሎቶች ዙሪያ የጋራ ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንደሚያመቻችም አስታውቋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ፈላጊዎች ወደ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ኢንፊኒቲ ደሴ ቅርንጫፍ
ህብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us