የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራትን (SACCOs) በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለመ ሀገር አቀፍ አውደ-ጥናት ተካሄደ፡፡

የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራትን (SACCOs) በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለመ ሀገር አቀፍ አውደ-ጥናት ተካሄደ፡፡
የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራትን (SACCOs) በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለመ ሀገር አቀፍ አውደ-ጥናት ተካሄደ፡፡
(ኢንፊኒቲ፡ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም)
በአዲስ አበባ ሐያት ሬጀንሲ ሆቴል በተካሄደው በዚህ አውደ ጥናት በርካታ ሀገር አቀፍ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ተሳትፈዋል፡፡
ከነዚህ ተቋማት አንዱ የሆነው ኢንፊኒቲ ኃ/የተ/መ/ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር (Infinity SACCOs) ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ እስክንድር መኩሪያ እንዲሁም ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ምስጋናው አየለ በአውደ-ጥናቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ኢንፊኒቲ በኢትዮጵያ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ዘርፍ ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ እውን በማድረግ አሰራሩን በማዘመን ላይ ይገኛል።
በፒትሮን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ (Pitron Technology Solutions PLC) የተዘጋጀውና "ቴምኖስ ኮር ባንኪንግ ኤግዚኩቲቭ ወርክሾፕ" የተሰኘው ፕሮግራም በዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በኅብረት ስራ ማኅበራት አመራር እና እድገት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በፒትሮን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ የተጋበዘውና በባንኪንግ ቴክኖሎጂ ከ150 ሀገራት በላይ እንደሚሰራ የተገለጸው የቴምኖስ ቡድን ለማኅበራት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቴክኖሎጂ የሚመራ (Technology-Driven) አሰራሮችና አገልግሎቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ኢንፊኒቲ በዚህ ሀገር አቀፍ ወርክሾፕ መሳተፉ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራሮችን ልምድ ለመቅሰምና የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል የማኅበሩን አባላት ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚረዳው በዝግጅቱ ላይ የተሳተፉት የማኅበሩ አመራሮች ገልጸዋል፡፡
ኢንፊኒቲ የሚሰጠውን የአገልግሎት ተደራሽነትና ቅልጥፍና ለማሻሻል ከአቻ ተቋማት፣ እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
ኅብረት ለዘላቂ ልማት!
Chat With Us